Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በተለያየ ዘርፍ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከሶማሊያ ትራንስፖርትና ሲቪል አቪዬሽን ጋር በቱሪዝም፣ ንግድና ትራንስፖርት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ፡፡

በስምምነቱ ላይ÷ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዳይሬክተር ጀኔራል ጌታቸው መንግስቴ እንዲሁም የሶማሊያ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቪዬሽን ሚኒስትር ፊርዶዋስ ኦስማን ኤጋል ተገኝተዋል፡፡

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ እንደገለጹት ፥ ስምምነቱ ሀገራቱ በአቪዬሽን ዘርፉ ያላቸውን ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ያግዛል፡፡

በተጨማሪም ሀገራቱ በትብብር የ2063 ግብን እንዲያሳኩ ስምምነቱ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመው÷ መንግሥት ስምምነቱን ለመተግበር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ጌታቸው መንግሥቴ እንዳሉት ስምምነቱ÷ የሀገራቱን ግንኙነት በቱሪዝም፣ በንግድና ትራንስፖርት ዘርፎች ለማጠናከር ያስችላል።

ፊርዶዋስ ኦስማን ኤጋል በበኩላቸው÷ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በማጠናከር በትራንስፖርት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ ለመውሰድ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.