Fana: At a Speed of Life!

የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተገኘበት ነው-አቶ አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተግበር ላይ የሚገኘው የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ።

ሚኒስትሩ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ለሚሲዮን መሪዎች የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ እና የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ዙሪያ ገለፃ ሰጥተዋል ።

ሚኒስትሩ በገለፃቸው÷ በመተግበር ላይ የሚገኘው የአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን ተናግረዋል።

በአገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያገጠሙ ምጣኔ ሃብታዊ ተግዳሮቶች በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፋቸውን የገለፁት አቶ አህመድ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ግጭት በማቆም የሰላም ስምምነት መፈረሙ ለኢኮኖሚው እድገት መልካም እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

የተፈጠሩትን ምቹ እድሎች ለሃገራዊ እድገቱ በመጠቀም ረገድ የሚሲዮን መሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ማስገንዘባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ የልማትና የኢኮኖሚ ትብብሮች እንዲጠናከሩ በማድረግ እንዲሁም ሀብትን በማሰባሰብ ጠንካራ ስራ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.