Fana: At a Speed of Life!

በንብረት ላይ የሚጣል ታክስ ስልጣን ለክልሎች ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ባካሄዱት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ የጋራ ልዩ ስብሰባ በንብረት ላይ የሚጣል ታክስ ስልጣን ለክልሎች እንዲሰጥ ተወሰነ፡፡

የሁለቱ ምክር ቤቶች አፈጉባዔዎች በመሩት በዚሁ ጉባኤ÷ በንብረት ላይ የሚጣለውን ታክስ ባለቤትነት አስመልክቶ የውሳኔ ሐሳብ ከቀረበ በኋላ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የውሳኔ ሐሳቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡

በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ መሰረት በንብረት ላይ የሚጣል ታክስ ስልጣን ለክልሎች የሚሰጥ ሆኖ÷ ክልሎች ደግሞ ባላቸው ሕገመንግስታዊ ስልጣን ለአካባቢ መስተዳድሮች እንዲሰጡ የሚል ሐሳብ የቀረበበት ነው፡፡

በከተሞች እና በክልሎች ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማስፈን፣ ሌብነትን ለመከላከል፣ የታክስ አማራጮችን ለማስፋት፣ ክልሎች ከድጎማ ተላቅቀው የመልማት ዕድላቸው እንዲሰፋ፣ ለከተሞች የመሰረተልማት አቅርቦትና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለማጠናከር እና በከተሞች የሥራ አጥነት ችግር እንዲቀረፍ የሚያግዝ የውሳኔ ሐሳብ ስለመሆኑ ተብራርቷል፡፡

የውሳኔ ሐሳቡ ቁጥር 1/2015 ሆኖ በ4 ተቃውሞ እና በ5 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ መጽደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.