Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብና የብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ሃሳብ ፥ በወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲሁም በጋራ ከተማችንን ስለምናለማበት ሁኔታ ፍሬያማ ውይይት ከደጋፊዎቹ ጋር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በስፖርት ማዘውተርያ ቦታዎች፣ በስራ እድል ፈጠራና በመልካም አስተዳደር ዙርያ ወጣቶቹ ያነሷቸውን ጥያቄዎችና ሃሳቦች ወስደን የሚታረመውን አርመን፤ የሚስተካከለውን አስተካክለን በጋራ ለመፍትሄው እንደምንረባረብ ላረጋግጥችሁ እወዳለሁም ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች ሃሳባቸውን በሰለጠነና በሰከነ መንገድ የሚያንፀባርቁ እንጂ በአመፅ ወይንም የሌላ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው አካላት መጠቀሚያ ሊሆኑ እንደማይፈልጉ ማረጋገጣቸውንም ነው ያነሱት፡፡

ከሌሎች የከተማዋ ወጣቶች ጋር ተከታታይ መድረኮችንና ውይይቶችን ማድረግ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣቶች የከተማችን የሰላምና የለውጥ ተምሳሌት ሆነው ይቀጥላሉም ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.