Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች ፕሪሚየር ሊግና የሴቶች ከፍተኛ ሊግ 2ኛ ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ፣ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድር የሚጀመርበት ቀን እና የዝውውር ጊዜ ይፋ ተደርጓል።
 
በዚህ መሰረትም የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እና ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድር የካቲት 26 ቀን2015 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡
 
የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በባህር ዳር ፤ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ደግሞ በሀዋሳ እንደሚካሄድም የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከጥር 17 እስከ የካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ደግሞ የዝውውር ጊዜ እንዲሆን መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡
 
በሌላ በኩል ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር መጋቢት 17 ቀን 2015ዓ.ም እንዲጀመር ሲወሰን÷ ከየካቲት1 እስከ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም የዝውውር ጊዜ እንዲሆን መወሰኑ ተገልጿል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.