Fana: At a Speed of Life!

አንዳንድ የጥበቃ ሰራተኞች ወንጀል ለመፈጸም በማሰብ በሃሰተኛ ሰነድ በተቋማት እየተቀጠሩ ነው – ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋማት የሚቀጥሯቸውን እና የቀጠሯቸውን የጥበቃ ሰራተኞች ማንነት በሚገባ መፈተሽ እና ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡
 
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጥበቃ አቅራቢ ኤጀንሲ ተወካዮች እና ከፋይናንስ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር በተለያዩ የግል እና የመንግስት ተቋማት እየተከናወነ በሚገኘው የጥበቃ ስራ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡
 
በውይይቱ መክፈቻ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት÷ አንዳንድ የጥበቃ ሰራተኞች ወንጀል ለመፈፀም በማሰብ በሃሰተኛ ሰነድ ጭምር በተለያዩ ተቋማት እየተቀጠሩ እንደሚገኙ በዳሰሳ ጥናት ተረጋግጧል፡፡
 
በዚህ መልኩየተቀጠሩ የጥበቃ ሰዎችም በተጨባጭ ወንጀል ሲፈፅሙ እንደተያዙ ነው ከሚሽነሩ የተናገሩት፡፡
 
ተቋማት የሚቀጥሯቸውን እና የቀጠሯቸውን የጥበቃ ሰራተኞች ማንነት ሊያረጋግጡ እና በዚህ በኩል የጥበቃ አቅራቢ ኤጀንሲዎችም ግዴታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
 
ከሰው ሃይል ቅጥር፣ በቂ ተያዥ ከማቅረብ እና የተሟላ መረጃ ከመያዝ ጋር በተገናኘ በኤጀንሲዎች በኩል የሚታዩ ክፍተቶ ሊታረሙ እንደሚገባ መገለጹን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃያመላክታል፡፡
 
የውይይቱ ተሳታፈዎች በአንዳንድ የጥበቃ ሰራተኞች አማካይነት የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የጥበቃ አቅራቢ ኤጀንሲዎች የሚጠበቅብንን ሃላፊነት በመወጣት በጋራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.