Fana: At a Speed of Life!

ከ376 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ለማስጀመር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ376 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በሲዳማ ክልል ዳየ ከተማ ለማስጀመር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ  አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ፥ ዜጎችን የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የበንሳ ዳየ ከተማ  የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ያለበት በመሆኑ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ የህብረተሰቡን ችግር እንዲቀርፍ ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው ያስገነዘቡት፡፡

አምባሳደሩ ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የግንባታ ስራውንና የግብዓት አቅርቦቱን ጂቲቢ ኢንጂነሪንግና ኢሙ አጠቃላይ አስመጪ በጋራ የሚያከናዉኑ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.