የሀገር ውስጥ ዜና

ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሱ

By Alemayehu Geremew

January 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 1 ሺህ 27 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በሦስት ዙር በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኞችን የመመለስ ተግባር 1 ሺህ 27 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ከሕዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ 27 ሺህ 722 ኢትዮጵያውያን ተመልሰዋል፡፡