Fana: At a Speed of Life!

ለወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በግጭት ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት የወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ተደረገ፡፡

ድጋፉ የተደረገው በሂውማን ብሪጅ ግብረሰናይ ድርጅት አማካኝነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ በድጋፍ እርክክቡ ላይ የጤናው ዘርፍ በግጭቱ ምክንያት ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት ገልጸዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ያጋጠሙትን ችግሮች በመቅረፍ የተሟላ የቀዶ ጥገና፣ የምርመራ እንዲሁም ለጨቅላ ሕፃናት አገልግሎት በተሟላ መልኩ ለመስጠት እየተደረገ ያለውን ጥረት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የሂውማን ብሪጅ ካንትሪ ዳይሬክተር ዶክተር አዳሙ አንለይ ÷ ድርጅቱ ዛሬ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ለሌሎች ጉዳት ለደረሰባቸው ተቋማት ድጋፍ አድርጓል ማለታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.