Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት 6 ወራት 33 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከ33 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ÷ የ2015 በጀት የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የስራ አፈጻጸምን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት አጋማሽ 33 ነጥ 8 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት የእቅዱን 96 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በቴሌብር አገልግሎት 27 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን በማፍራትና በስድስት ወራት ውስጥ 166 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የየግብይት መጠን በማንቀሳቀስ የ82 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ገቢ ማግኘት መቻሉንም አንስተዋል፡፡

የተገኘው ገቢ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ19 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው ያስረዱት፡፡

በዚህም 5 ነጥብ 62 ቢሊየን ብር እድገት እንዳለው የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ÷ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 64 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ጠቁዋመል፡፡

የተገኘው የገቢ ድርሻ በአገልግሎት አይነት ሲታይ የድምፅ አገልግሎት 47 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ ሲኖረው ዳታና ኢንተርኔት 28 በመቶ ፣ ዓለም አቀፍ ገቢ 8 ነጥብ 4 በመቶ ፣ የመሰረተ ልማት ኪራይ 2 ነጥብ 2 በመቶ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች 7 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ተመላክቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፋት6 ወራት ደንበኞቹን ወደ 70 ሚሊየን ከፈ ያደረገ ሲሆን÷ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር የ15 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንዳለውም ጠቁመዋል።

በማህሌት ተክለብርሃን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.