Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ጋር  ተወያይተዋል፡፡

እንዲሁም ከንቲባዋ ከአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ሊዲያ ግርማን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም በመዲናዋ በሰላም እና በአብሮነት ዕሴት ዙሪያ በጋራ መሰራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

በውይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ መጋቢ አእላፍ በላይ ፀጋዬ እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ መሳተፋቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.