Made with LogoLicious Add Your Logo App

የሀገር ውስጥ ዜና

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሰሜን ምዕራብ እዝን ጎበኙ

By Amele Demsew

January 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሰሜን ምእራብ ዕዝ ደረጃ ሶስት ሆስፒታልን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተጨማሪ ሌሎች የኢፌዴሪ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ከፍተኛ የጦር ጄኔራል መኮንኖች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

ሀገርን ለማጽናት የተዋደቁ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ሕዝባችንን ይዘን የማንፈፅመው ተልዕኮና የማንወጣው ግዳጅ የለም፤ የተሰዋነው እና የቆሰልነው ለሕዝባችን ደኅንነት እና ለሕዝብ አንድነትና ክብር ነው ነው ሲሉም ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል ።

አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩዋትን ሀገር በደማችን እና በአጥንታችን አስከብረን ለትውልድ እናስተላልፋለን ሲሉም መልእክት ማስተላለፋቸውን አሚኮ ዘግቧል ።