ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ከፈረንሳይና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪ ኮሎናን እና ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባኤርቦክ ጋር ተወያዩ፡፡
ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የሚገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ከፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ጋር በነበራቸው ውይይት÷ የሀገራቱን ረጅም ዘመን የዘለቀ ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
በመንግሥትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሚደረገው የመልሶ ግንባታ ሥራ÷ ሀገራቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሚኒስትሮቹ አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የመልሶ ማቋቋምና የድጋፍ ሥራዎች ሴቶችን ታሳቢ ማድረግ እንደሚገባቸውም ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!