Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ማጠናከር ትፈልጋለች-ትሬሲ ጃኮብሰን

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ማጠናከር ትፈልጋለች ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ተናገሩ፡፡

ለስራ ጉብኝት ጅማ ከተማ የሚገኙት ትሬሲ ጃኮብሰን÷ በከተማዋ እና አካባቢው ያሉ ምቹ  የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ትሬሲ ጃኮብሰን በጅማ ዞንናበኦሮሚያ ክልል አመቺ የቡና ልማት መኖሩን ጠቅሰው÷ ሀገራቸው በኢኮኖሚና  በኢንቨስትመንት ዘርፍ  ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል ያለው የሰላም ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱንና ለዚህም አሜሪካ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

በኮቪድ-19 ምክንያት ለሁለት ዓመታት ተዘግቶ የቆየው አሜሪካን ኮርነር ቤተመጽሓፍ በአምባሳደሯ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ ተመላክቷል

 

በሙክታር ጣሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.