Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲው 200 ኢትዮጵያውን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ 200 ኢትዮጵያውን  ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ የኬንያን ድንበር አቋርጠው የገቡ  መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ስለሆነም በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድጋፍ ክሳቸው ተቋርጦና ከእስር ቤት ተፈተው በምህረት  ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ላንጋታ፣ ኢንደስትሪያል፣ ማኮንጊ፣ ካሳራኒ፣ እና ካዩሌ በተባሉ እስር ቤቶች ከሁለት እስከ ስድስት ወራት ድረስ በእስር ላይ የቆዩ ናቸው ተብሏል፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን መብት ለማስከበር ከሀገሪቱ የኢሚግሬሽን ኃላፊዎች እንዲሁም ከኬንያ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት ጋር በቅርበት ተባብሮ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ቀደም ሲልም በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ከእስር ተለቀው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ኤምባሲው ድጋፍ ማድረጉን ከኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.