Fana: At a Speed of Life!

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዋን አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ማሪቱ ለገሠ ከሰባት ዓመታት በፊት ሰጥቷት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በዛሬው ዕለት አስረክቧል።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ አርቲስት ማሪቱ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ላበረከተችው አስተዋጽኦ በ2008 ዓ.ም የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷት እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለትም አርቲስቷ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዋ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የተረከበች መሆኑ ተገልጿል፡፡

አርቲስት ማሪቱ ለገሰ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በተሻገረው የሙዚቃ ህይወቷ አራቱን የሙዚቃ ቅኝቶች በመጫወት ትታወቃለች፡፡

በተለይም የአምባሠል ቅኝት አጨዋወቷ የመጠሪያዋ ቅጽል ስም እስከመሆን አድርሷታል ።

ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ አርቲስት ማሪቱ በወሎ ላሊበላ የኪነት ቡድን ውስጥ በመሆን በአምባሰል፣ አንቺ ሆዬ፣ ባቲ እና ትዝታ ሙዚቃዎች አይረሴ ስራዎችን ተጫውታለች።

አርቲስቷ ዓመቱን ሙሉ የባህል አልባሳት በመልበስ በባህል አምባሳደርነትም ትታወቃለች።

በሰላማዊት ተስፋየ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.