Fana: At a Speed of Life!

 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ማራቶን ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች እንደሚሳተፉ የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡

በወንዶች ምድብ ሌሊሳ ዴሲሳ፣ሹራ ቂጣታ፣ አንዳምላክ በልሁ ፣ አንዱዓለም በላይ እንዲሁም ሂርጳሳ ነጋሳ በውድድሩ ይካፈላሉ፡፡

በሴቶቹ ደግሞ የዓለም የማራቶን ሻምፒዮኗ  ጎይተይቶም ገብረስላሴ  እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት አማኔ በሪሶ በውድድሩ ይሳተፋሉ።

በተጨማሪም አባብል የሻነህ፣ አፀደ ባይሳ እና ህይወት ገብረ ማሪያም በ2023ቱ በቦስተን ማራቶን የሚሳተፉ አትሌቶች ናቸው፡፡

በ127ኛው የቦስተን ማራቶን ውድድር በወንዶች ምድብ የዓለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌን ጨምሮ የባለፈው ዓመት በውድድሩ ሁለተኛ የወጣው ታንዛኒያዊ አትሌት ጋብሬክ ጌይ ይካፈላሉ።

በሚያዚያ ወር በሚደረገው ውድድር ከ28 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይካፈላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የቦስተን ማራቶን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.