የወጋገን ባንክ 8 ተጨማሪ ቅርንጫፎች ዳግም አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋገን ባንክ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው በቆዩት በመቀሌ እና ሽረ ዲስትሪክቶች በሚገኙ ተጨማሪ ስምንት ቅርንጫፎቹ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
በዚህም በመቀሌ ዲስትሪክት÷ በውቕሮ፣ አጉላዕ፣ ዓዲ ጉደም፣ ዓዲ ሹምድሑን እና ክልተ አውላዕሎ እንዲሁም በሽረ ዲስትሪክት በእንዳባጉና ፣ ሰለኽለኻ እና ውቕሮ ማራይ ቅርንጫፎቹ ባንኩ ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በመቀሌ ዲስትሪክት በ38 ቅርንጫፎች እና በሽረ ዲስትሪክት በ22 ቅርንጫፎች በአጠቃላይ በ60 ቅርንጫፎቹ ዳግም አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡