የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት በሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ አስተባባሪነት የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ ልዑክ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር ዉይይት አካሄደ፡፡
የዓለም አቀፉ ሙስሊሞች ሊግ በአውሮፖ እና የአሜሪካ ዋና አስተባባሪና የኢስላሚክ ሊግ የዋና ፀሐፊው አማካሪ በሆኑት በዶ/ር አብዱልአዚዝ ሳርሃን የሚመራ ልዑክ ከሰላም ሚኒስቴር የሠላም ግንባታና የብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከሆኑት ከአቶ ታዬ ደንድአ ጋር ነው ዉይይት ያካሄዱት፡፡
የዓለም ዓቀፉ ሙስሊሞች ሊግ በቀጣይ በሀገራችን ሊሰራቸው ባቀዳቸው ሁሉን አቀፍ ሰላም፣ ጤና እና ትምህርት ላይም መክረዋል፡፡
ሚኒሰትር ዴዔታ ታዬ ደንደኣ ሚኒስቴሩ ከሊጉ ጋር በቀጣይ በጋራ ሊሠሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም ነው የገለጹት።
የአለም አቀፍ ሙስሊሞች ሊግ ልዑካን በቀጣይ ቀናትም ከሌሎች ሚኒስቴሮች ጋርም ዉይይት ያካሂዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!