Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት የማጠቃለያ ሥራዎች እየተከናወኑለት መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀደም ሲል የመዋቅር ግንባታ ሥራው የተጠናቀቀው የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት ግንባታ አሁን ላይ የተለያየ የማጠቃለያ ሥራዎች እየተከናወኑለት መሆኑ ተገለጸ፡፡

በአዲስ አበባ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽሕፈት ቤት የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዚየም ፕሮጀክት ተወካይ ኢንጅነር ፈለቀ ወ/ዮሐንስ እንደገለፁት÷የመዋቅር ግንባታ ሥራው መጠናቀቅን ተከትሎ የማጠቃለያ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

በዚህም የአሌክትሪክ መስመርና የውኃ መስመር ዝርጋታ፣ የወለል ንጣፍ ሥራዎች፣ የጅብሰም እና ሌሎች መሰል የማጠቃለያ ተግባራት በሕንጻው ውስጣዊ ክፍሎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አብራተዋል፡፡

አጠቃላይ ሙዚየሙን ለአገልግሎት ለማብቃት ሥራዎች እየተፋጠኑ ሲሆን÷ የፕሮጀክት ግንባታ አፈፃፀም ከ77 መቶ በላይ መድረሱ ተጠቁሟል፡፡

ይህ ዘመን ተሻጋሪ የግንባታ ዐሻራ አዲስ አበባ የእንቅስቃሴዎች ማዕከል መሆኗን ከማመላከቱ ባሻገር÷ ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ተሰባስበው ለድል የተነሱበትና ድል ያስመዘገቡበት ታላቅ ማስታወሻ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.