Fana: At a Speed of Life!

የቻን አፍሪካ ሀገራት ውድድር በዛሬው ዕለት ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጄሪያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 7ኛው የቻን አፍሪካ ሀገራት ውድድር በዛሬው ዕለት ይጀመራል፡፡
 
17 ሀገራት የሚሳተፉበት ይህ ውድድር በአልጄሪያ አራት ከተሞች በሚገኙ ስታዲየሞች እንደሚከናወን የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል፡፡
 
ውድድሩ ዛሬ በይፋ ሲከፈት አዘጋጇ አልጀሪያ ከሊቢያ ጋር ምሽት 4 ሰዓት ላይ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል፡፡
 
በውድድሩ ለመሳተፍ ትናንት አልጀሪያ የገባው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደግሞ በነገው ዕለት ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ቀን 10 ሰዓት ላይ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡
 
ብሔራዊ ቡድኑ በአልጀርስ የመጀመሪያ ልምምዱን ትናንት ምሽት ማከናወኑን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.