የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ነገ ፍጻሜውን ያገኛል
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)3ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የድምፃ ውያን ውድድር ነገ ፍጻሜውን ያገኛል፡፡
የአመቱን ሶስት ምዕራፎች በአሸናፊነት ያጠናቀቁ 12 ተወዳዳሪዎችና በልዩ ሁኔታ የተካተቱ ሁለት ተፎካካሪዎች በአጠቃላይ 14 ተወዳዳሪዎች ለ10 ሳምንታት ሲፎካካሩ ቆይተዋል፡፡
በዚህም አራት ተወዳዳሪዎች የተለዩ ሲሆን÷በነገው እለት የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊ ለመሆን ይፋለማሉ፡፡
በዚህም ደሳለኝ አበበ፣ አሉላ ገ/አምላክ፣ ዳንኤል አዱኛ እና ያለምወርቅ ጀምበሩ ተፋጠዋል፡፡
በርካታ ተመልካቾችና አንጋፋ አርቲስቶች በተገኙበት በቀጥታ ስርጭት በሚካሄደው የፍጻሜ ውድድርም አሸናፊው ይለያል፡፡
ከዚህ በፊት በተደረጉ ሁለት የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድሮች መቅደስ ግርማ እና አህመድ ሁሴን (ማን ጁስ ) ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ይህን አጓጊ ውድድር ለመከታተል የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ