Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ካለፉት ጊዜያት አንጻር እያደገ መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ካለፉት ዓመታት አንጻር በአፋር ክልል የኢንቨስትመንት ፍሰቱ ዕድገት ማስመዝገቡን የአፋር ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ፡፡

በኮሚሽኑ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እና መረጃ ዳይሬክተር ኢድሪስ ኢስማኤል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በነበረው ግጭት ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው ኢንቨስትመንት በያዝነው በጀት ዓመት ተነቃቅቷል፡፡

ይህም በአካባቢው የሰላም አየር መንፈሱን ተከትሎ ኮሚሽኑ ባለሃብቶችን ለመሳብ እና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው እንዲነቃቃ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤት መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡

በዚህም በያዝነው በጀት ዓመት በተጠናቀቀው 6 ወር ከ69 በላይ ባለሃብቶች በግብርና፣ በስንዴ ልማት፣ በጨው ማምረት፣ በእንስሳት እርባታ እና በመኖ ማቀነባበር ዘርፎች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጠናቀቀው ስድስት ወር የባለሃብት ቁጥር መጨመሩን እና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውም ከሌላው ጊዜ አንጻር ዕድገት እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ባለሃብቶችን ከመሳብ አኳያ ባለፈው ሙሉ ዓመት 56 ነጥብ 9 እንደነበር አስታውሰው÷ በዚህኛው በጀት ዓመት ስድስት ወር ግን 61 ነጥብ 9 መድረሱን ነው የተናገሩት፡፡

ይህም ካለፈው ሙሉ ዓመት አንጻር የዚህኛው በጀት ዓመት 6 ወር የተሻለ የኢንቨስትመንት ፍሰት የታየበት መሆኑን ያሳያል ነው ያሉት፡፡

በስድስት ወሩ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ ከ69 በላይ ባለሃብቶች 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገደማ ካፒታል ማስመዝባቸውንም ነው የገለጹት፡፡

በዚህም በተለያዩ ዘርፎች ለ2 ሺህ 977 ገደማ ወገኖች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.