የየክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ።
በጉብኝቱም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
አፈ-ጉባኤዎቹ ከዋናው የህዳሴ ግድብ በተጨማሪ የኮርቻ ግድቡን የጎበኙ ሲሆን÷ስለግድቡ አጠቃላይ ማብራሪያ እንደተደረገላቸው ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡