Fana: At a Speed of Life!

የአኮቦ ወርቅ ፋብሪካ ከ3 ወራት በኋላ ምርት እንደሚጀምር ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአኮቦ ወርቅ ፋብሪካ ከሦስት ወራት በኋላ ምርት እንደሚጀምር የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ዑማ ገለጹ።

ኢንጂነር ታከለ ዛሬ ከፌደራል እና ከጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የአኮቦ የወርቅ ፋብሪካ የተከላ ሒደትን ጎብኝተዋል፡፡

የወርቅ ፋብሪካው በዓመት ከ 100 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚያስገኝ ኢንጂነር ታከለ ዑማ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል፡፡

ፋብሪካው ምርት ሲጀምር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተጨማሪ አቅምን የሚፈጥር፣ የግሉ ዘርፍ የማዕድን ኢንቨስትመንትም የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በወርቅ ማዕድን ዘርፍ  የተሰማሩ ኩባንያዎች ለዘርፍ ማደግና ለወርቅ ሃብት ክምችቱ ማደግ እንዲረዳ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በጋምቤላ አኮቦ፣ በቤኒሻንጉል፣ በትግራይ ሽረ፣ በሻኪሶ ያሉ የወርቅ ኩባንያዎች ተደማምረው የኢትዮጵያን የወርቅ ምርት ከ3 ዓመታት በኋላ ወደ 30 ቶን እንደሚያሳድጉ ተጠቁሟል፡፡

የአኮቦ ወርቅ ፋብሪካ ሥራ ከአንድ ዓመት በፊት በጋምቤላ ክልል በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.