Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በአህጉራዊ ጉዳዮች ትብብራቸውን ለማጠናከር እየሠሩ ነው – አምባሳደር ሙክታር ከድር

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ከሁለትዮሸ ባሻገር በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እየሠሩ መሆኑን አምባሳደር ሙክታር ከድር ገለጹ፡፡

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድርኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በንግድ፣ በኢንቨስትመት፣ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና በሌሎች ዘርፎች በትብብር እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት መድረክ ከማስተናገድ ባሻገር ሂደቱ ምቹ እንዲሆን ደቡብ አፍሪካ የላቀ ሚና መወጣቷን አስታውሰዋል። በዚህም የሰላም ስምምነቱ “ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በማመንጨት” ስኬት የተመዘገበበት መድረክ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

በቀጣይም ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርግ ጠንካራ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ለመመስረት እንቅስቀሴዎች መጀመራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሀገራቱ ከሁለትዮሸ ግንኙነት በተጨማሪ በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ የጋራ አቋም በመያዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሠሩ እንደሚገኙ አምባሳደር ሙክታር ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካውያን የአፓርታይድ ስርዓት ያስከተለባቸውን ችግር በውይይት ፈትተው የተሻለ ሀገር መገንባታቸውን ጠቅሰው÷ ይህ ልምድ ኢትዮጵያ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ለምታደርገው ጥረት ይጠቅማል ብለዋል፡፡ በተለይም ለሀገራዊ ምክክር ስኬታማነት የሚጠቅም በመሆኑ ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ዘርፈ ብዙ ልምዶችን እንደምትቀስም ነው የገለጹት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.