Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ሥምምነቶችን ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶችን አዲስ አበባ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ተፈራርመዋል፡፡
 
የመጀመሪያው የፋናንስ ድጋፍ ሥምምነት የ32 ሚሊየን ዩሮ ሲሆን÷ ድጋፉ በግጭት በተጎዱ የአማራ፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ የኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻል እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋጋጥ የሚውል ነው ተብሏል፡፡
 
ሁለተኛው ስምምነት ደግሞ የ10 ሚሊየን ዩሮ የፋይናስ ድጋፍ ሲሆን÷ 6 ሚሊየን ዩሮው አዲስ የፋይናነስ ድጋፍ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
 
ቀሪው 4 ሚሊየን ዩሮ ደግሞ ከዚህ ቀደም ለኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላላፊያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተሰጠውን ብድር ለማራዘም የተደረገ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
 
በስምምነቱ መሠረት እስከ ፈረንጆቹ ታኅሣሥ 31 2024 ባለው ጊዜ ውስጥ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክትን ለማስፈጸም ያስችላል፡፡
 
የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶቹን በኢትዮጵያ በኩል የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይና የአውሮፓ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎና ተፈራርመዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.