ስፓርት

ኢትዮጵያ የፊታችን እሑድ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ጉባኤን ታስተናግዳለች

By Mikias Ayele

January 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተካለሉበት የአትሌቲክስ ሪጅን ጉባኤ የፊታችን እሑድ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይካሄዳል፡፡

በጉባኤው የሪጅኑ ፕሬዚዳንት፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫና በሪጅኑ የኮንፌዴሬሽን ኦፎ አፍሪካ አትሌቲክስ ካውንስል አባላት ውክልና እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በዞኑ በአትሌቲክስ ልማትና እንቅስቃሴ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርትና የቀጣይ ዓመት የስራ እቅድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል፡፡

በፈረንጆቹ አቆጣጠር  ጥር 12 ቀን 2019 በአዲስ አባባ በተደረገው የሪጅኑ ስብሰባ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ምክትል ሊቀመንበር ሆና መመረጧ ይታወሳል፤ እስከአሁንም እያገለገለች ትገኛለች፡፡

እሑድ በሚደረገው ጉባኤ የባህልና ስፖርት ሚኒስትርና የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው እንዲሁም የኮንፈዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት  ሃማድ ካልካባ ማልቡም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡