የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 27 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

January 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 27 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 942 ወንዶች፣ 61 ሴቶች እና 24 ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እመሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡