Fana: At a Speed of Life!

ከ168 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከታኅሣሥ 28 እስከ ጥር 4 ቀን 2015 ባደረገው ክትትል 86 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የገቢ እና 82 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡

ከ168 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የተያዙት በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በተደረገ ክትትል ነው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ÷ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 12 ግለሰቦች እና ስድስት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከጉምሩክ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.