Fana: At a Speed of Life!

በተጠናቀቀው 6 ወር ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ለኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ የሚሆን ከ85 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት መዘጋጀቱንም ተጠቁሟል፡፡

የሥራ እና ክኅሎት የሥራ እና ስምሪት ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን ለኢዜአ እንደተናገሩት ÷ ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ ብቻ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4 ቢሊየን ብር ስምምነት ተደርጓል፡፡

በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ለ3 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ከ285 ሺህ በላይ አዳዲስ ኢንተርፕራይዞችን የመመስረት ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.