የሀገር ውስጥ ዜና

ከአዲስ አበባ መቀሌ ዕለታዊ የበረራ ብዛት ቀንሷል የሚለው የተሳሳተ መረጃ ነው- አየር መንገዱ

By ዮሐንስ ደርበው

January 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባ መቀሌ ዕለታዊ የበረራ ብዛት ቀንሷል የሚለው የተሳሳተ መረጃ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገገድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመቀሌ በረራውን ከጀመረ ጊዜ አንስቶ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ እና ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞችን ማገልገሉን እንደቀጠለ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከዕድሜ ጋር ተያይዞ ተጓዦች ላይ የጣለው ምንም አይነት የበረራ ገደብ አለመኖሩንም ነው በመግለጫው የተመላከተው፡፡

ወደ መቀሌ የሚደረገው በረራም በቀን ወደ ሦስት ከፍ ማለቱን እና ዕለታዊ የበረራ ብዛት ቀንሷል የሚለው የተሳሳተ መረጃ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ወደፊትም የሚኖረውን የበረራ ፍላጎት እያየን የበረራውን ብዛት ለመጨመር ዝግጁ ነን ብሏል አየር መንገዱ፡፡