የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ምርቶችን ለውጭ ከሚያቀርቡ ላኪዎች ጋር ተወያየ

By Meseret Awoke

January 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ ምርቶችን ለውጭ ገበያ ከሚያቀርቡ ላኪዎች ጋር በክልሉ ፕሬዚደንት ፅህፈት ቤት ተወያይቷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት ሽመልስ አብዲሳ ፥ አንድ ሀገር የሚከበረው ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባት ስትችል በመሆኑ የሀገራችንን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የላኪዎች ሚና ጉልህ ነው ብለዋል፡፡

ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ባለሀብቱ እና መንግስት በጥምረት መስራት አስፈላጊ እንደሆነም ነው ያነሱት፡፡

ባለሀብቱ በፍፁም የሀገር ፍቅር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ከምንገዜውም በላይ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ፥ መንግስት በውጭ ንግድ ላይ የሚስተዋለውን ህገ- ወጥ ንግድ ለመቆጣር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሰራ መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!