ስፓርት

ኢትዮጵያ ከሞዛምቢክ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ ያለምንም ግብ አጠናቀቀች

By Tamrat Bishaw

January 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ7ኛው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒየን ሺፕ ቻን ውድድር የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋን ከሞዛምቢክ ጋር ያደረገችው ኢትዮጵያ ጨዋታዋን ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት አጠናቃለች።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቻ መውጣቱን ተከትሎ አንድ ነጥብ በመያዝ በምድቡ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

7ኛው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒየንሺፕ ውድድር በኮቪድ-19 ምክንያት ነበር ከፈረንጆቹ 2022 ወደ 2023 የተዘዋወረው።