ስፓርት

በማንችስተር ደርቢ ዩናይትድ ሲቲን 2 ለ1 አሸነፈ

By Tamrat Bishaw

January 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ የማንችስተር ደርቢ ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ማርከስ ራሽፎርድ እና ፈርናንዴዝ ሲያስቆጥሩ የማንችስተር ሲቲን ግብ ግሪሊሽ አስቆጥሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በተከታታይ ያደረጓቸውን ሰባት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት በማጥበብ በ38 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሽንፈት ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ ደግሞ ሰላሳ ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በኦልትራፎርድ በተደረገው አስደናቂ ደርቢ ከኋላው በመምጣት ማንቸስተር ሲቲን በማሸነፍ አስደናቂ ለውጥ አድርጓል።