የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ በ90 ቀናት እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

By Meseret Awoke

January 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ በ90 ቀናት እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

ከንቲባዋ በለሚ ኩራ በ90 ቀናት እየተከናወኑ የሚገኙ የመንገድ አካፋይ የአረንጓዴ ልማት፣የአቅመ ደካሞች የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የእንጀራ ማምረቻ ማዕከል፣የወተት ከብት እርባታ ፣ኮንቬንሽን ማዕከል እንዲሁም አዲሱን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ህንፃንና የመንገድ የመሠረተ ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ነው የጎበኙት።

በጉብኝታቸውም ፥ በክፍለ ከተማው በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አድነቀዋል፡፡

በቀሪ ስራዎች ላይም በተሻለ ትጋትና ቁርጠኝነት በመስራት በጋራ የምናስበው ስኬት ላይ መድረስ እንደሚቻል በጉብኝቱ ወቅት ገልጸዋል።

በክፍለ ከተማው እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች በበጎ ፍቃደኛ ሀገር ወዳድ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች እንደሆነ መገለጹን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!