Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ተሾሙ፡፡

አቶ ጥላሁን ከበደ በትምህር ዝግጅት ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው ሲሆን፥ በቀድሞ የጋሞ ጎፋ ዞን ከወረዳ አመራሪነት አንስቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪነት አገልግለዋል።

ከ2008 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ የደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው እስኪሾሙ ድረስም በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

በተጨማሪም የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል መሆናቸውን ከደቡብ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.