ስፓርት

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ዛሬ ወደ ውድድር ትመለሳለች

By ዮሐንስ ደርበው

January 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የረጅም ርቀት ሯጯ ጥሩነሽ ዲባባ ከአራት ዓመታት በኋላ ዛሬ በአሜሪካ በሚካሄደው የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ወደ ውድድር ትመለሳለች።

የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ እና የአምስት ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው አትሌት ጥሩነሽ ባለፉት አራት ዓመት ምንም አይነት ውድድር አድርጋ አታውቅም።

ዛሬ ለ22ኛ ጊዜ በሚካሄደው የሂውስተን ማራቶን ከሚሳተፉ አትሌቶች መካከል ጥሩነሽ ዲባባ ትገኝበታለች።

አትሌት ጥሩነሽ በርቀቱ ያስመዘገበችው ፈጣን ሰዓት በፈረንጆቹ በ2017 በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በተካሄደው የራስ አልካይማህ ግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ያስመዘገበችው ነው።

በውድድሩ ላይ የጥሩነሽ ታናሽ እህት አና ዲባባን ጨምሮ አትሌት ሕይወት ገብረኪዳን እና አትሌት አፀደ ባይሳ ይሳተፋሉ፡፡

በሌላ በኩል አትሌት ሹራ ቂጣታ እና አትሌት ልዑል ገብረስላሴ በወንዶች ግማሽ ማራቶን ከሚሳተፉ አትሌቶች መካከል መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም ነገ በስፔን ቫሌንሺያ በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት የዓለምዘርፍ የኋላው ውድድሩን የማሸነፍ የቅድሚያ አግኝታለች።

በዓለም አትሌቲክስ የወርቅ ደረጃ በተሰጠው የጎዳና ላይ ውድድር የኬንያ እና ዩጋንዳ አትሌቶች የዓለምዘርፍ ዋነኛ ተፎካካሪ መሆናቸው ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!