Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ280 በላይ ተጠርጣሪዎች ከነኤግዚቢቶቻቸውበቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተደጋጋሚ ወንጀሎችን በሚፈፅሙ ግለሰቦች እና ወንጀል በሚፈፀምባቸው ቦታዎች ላይ በተከናወነ ሥራ ከ280 በላይ ተጠርጣሪዎች ከነ ኤግዚቢቶቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የስርቆትና ደረቅ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ፣ በተፈፀሙ ወንጀሎች መነሻነት ብቻ ሳይሆን ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎችን አስቀድሞ በመለየት እና በፈፃሚዎች ላይ ጥናት አድርጎ የወንጀል እንቅስቃሴያቸውን ለመግታት በተከናወነ ሥራ ከ280 በላይ ተጠርጣሪዎች ከነኤግዚቢቶቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ መገናኛ ዙሪያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 15 ተጠርጣሪዎች የተያዙ ሲሆን÷ ከ113 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የሞባይል ስልኮችም በኤግዚቢትነት መያዛቸውን የአዲስ አበባ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ መገናኛ ዙሪያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 50 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና ከእነዚህ ውስጥ 35ቱ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል፡፡

200 የሞባይል ስልኮችም በተለያየ ጊዜ ተይዘው አብዛኞቹ ለባለቤቶቹ መመለሳቸው ነው የተጠቆመው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዋን ሠላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጾ÷ ወንጀልን ለመከላከል እንዲቻል ሕብረተሰቡ የሚሰጠውን ጥቆማ እና መረጃ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.