የሀገር ውስጥ ዜና

የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የምርጫ ኮንግረስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ

By Mikias Ayele

January 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረገው የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የምርጫ ኮንግረስ ለቀጣይ አራት ዓመታት ሪጅኑን የሚመሩ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጠዋል፡፡

በዚህ መሠረትም ጄነራል ጃክሰን ቲዊ ከኬንያ ፕሬዚዳንት ሆነው ሲመረጡ÷ ሚስተር ዶሚኒክ ኡትሲት ከኡጋንዳ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ተመርጠዋል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌደሬሽን ካውንስል አባል በመሆን ተመርጣለች፡፡

ዶክተር ኢንጂነር ሲዲቅ ኢብራሂም ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ዋና ጸሃፊና አቃቤ ንዋይ እንዲሁም የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌደሬሽን ካውንስል አባል በመሆን መመረጣቸውን የፌደሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡