Fana: At a Speed of Life!

በአቶ ካሳሁን ጎፌ የተመራ ልዑክ ከጅቡቲ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ የተመራ ልዑክ ከጅቡቲ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስትር አሊ ዳውድ ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ ዋና ዋና የወጪ ንግድ ምርቶች እና የንግድ ስምምነቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጀቡቲ የገባው የሁለቱ ሀገራት የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ቀድም ሲል  በኢትዮጵያ ባደረጉት ስብሰባ ያደረጓቸውን የንግድ ስምምነቶች ተከትሎ መሆኑን ከጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.