ስፓርት

በሂውስተን ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች  አሸነፉ

By Mikias Ayele

January 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በተካሄደው የሂውስተን ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጸታዎች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በሂውስተን የወንዶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ልዑል ገብረ ስላሴ አሸንፏል፡፡

አትሌት ልዑል ርቀቱን 1፡00፡34 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈው፡፡

በሴቶች ግማሽ ማራቶን ምድብ ደግሞ አትሌት ህይወት ገብረማሪያም ውድድሩን በቀዳሚነትጨርሳለች፡፡