ቢዝነስ

የአማራ ክልልን የቱሪዝም ዘርፍ ማነቃቃት ዓላማ ያደረገ የድንቅ ምድር እውቅናና የቁንጅና ውድድር ተካሄደ

By Mekoya Hailemariam

January 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልልን የቱሪዝም ዘርፍ ማነቃቃት ዓላማ ያደረገ “የድንቅ ምድር እውቅናና ሽልማት” እንዲሁም የቁንጅና ውድድር ተካሄደ።

ከፍተኛ የክልሉ የሥራ ኅላፊዎች በተገኙበት በጎንደር  ከተማ አጼ ፋሲል ቤተ መንግሥት ስነስርዓቶቹ ተካሂደዋል፡፡

በዚሁ መሠረትም የመጀመሪያውን የድንቅ መዳረሻ የእውቅና ሽልማት ላሊበላ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር እና ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አሸናፊ በመሆን ተመርጠዋል።

ቀጥሎ በተካሄደው “የወይዘሪት ቱሪዝም አማራ” የቁንጅና ውድድር ከሰሜን ሸዋ ዞን ቤዛ ሳህሌ አሸናፊ ሆናለች።

የውድድሩ አሸናፊ “ወይዘሪት ቱሪዝም-አማራ” በመባል የአማራ ክልል የ2015 ዓ.ም የድንቅ ምድር አማራ የባህል አምባሳደር ሆና ተሰይማለች፡፡