የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

By ዮሐንስ ደርበው

January 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ሱለይማን ደደፎ የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

አምባሳደር ሱለይማን ከዚህ በፊት በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ባለሙስልጣን አምባሳደር በመሆን ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም አቶ መሃመድ ጀማል ሸሪፍ የተቋሙ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እና ወ/ሮ መሰረት ደስታ ገ/የሱስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ የምርምርና ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ከጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መመደባቸው ተገልጿል ፡፡

የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕን በዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!