Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በ15ኛው የአቡዳቢ ዓለም አቀፍ የ“ሰስቴኒቢሊቲ” ሣምንት ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው በዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እና በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ በሚመክረው 15ኛው የአቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ “ሰስቴኔቢሊቲ” ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።

ኢኒሼቲቩ የዓየር ንብረት ለውጥን ለመግታት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ልማትን ዕውን ለማድረግ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ፣ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ዕድገትን ለማፋጠን ዓላማ አንግቦ በተባበሩት ዓረብ ኢሜሬቶች እና ማስዳር ከተማ ውስጥ በሚገኘው የታዳሽ ኃይል ማመንጫ የተጀመረ ነው፡፡

በዓየር ንብረት ለውጥ እና በታዳሽ ኃይል ላይ ሊመክር የተሰናዳው መርሐ-ግብር የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ የታደሽ ኃይል ተጠቃሚነት በዓለምአቀፍ ደረጃ እንዲሰፋ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው ተብሏል፡፡

መድረኩ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በኃይሉ ዘርፍ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት በመተባበር ለመሥራት ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያረጋግጥ ተጠቁሟል፡፡

በአየር ንብረት ለውጥ እና ታዳሽ ኃይል ላይ የሚመክረው የአቡ ዳቢው ጉባዔ “የዓየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመግታት እንተባበር” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባዔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ልዑካቸውን ጨምሮ የሀገራት መሪዎች ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ፣ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መሪዎች በአጠቃላይ 30 ሺህ ያህል ሰዎች ይሳተፋሉ።

መርሐ-ግብሩ በአየር ንብረት ለውጥ ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በውጤታማ የውሃ አጠቃቀም፣ በአሁናዊ የኢንዱስትሪ አካሄድ እና ዕድሎች እንዲሁም በዘላቂ ቆሻሻ አወጋገድ እና ስማርት ከተማ ላይም ይመክራል ተብሏል።

በጤና ፣ በምግብ ፣ በኃይል፣ በውሃ አጠቃቀም እና በዓለም አቀፍ የሁለተኛ ትምህርት ቤቶች ዘርፍ ለሰው ልጆች የላቀ የፈጠራ ሥራ ለሰሩ ÷ የ“ዛይድ ሰስቴኔብሊቲ” ሽልማት መበርከቱ ተገልጿል።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ የሚካሄደውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ28) እንድታስተናግድ መመረጧ ይታወሳል።

በአልዓዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.