Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል ኃይማኖታዊ እሴቱን  ጠብቆ እንዲከበር የመዲናዋ ነዋሪ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የአዲስ አበባ ነዋሪ የበኩሉን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጠይቋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ፥ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የጥምቀት በዓል በሰላም በሚከበርበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ በዚህ ወቅት የጥምቀት በዓል ከእምነቱ ተከታዮች በተጨማሪ የሌሎች እምነት ተከታዮችም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በሚያሳይ መልኩ በዓሉ በሰላም እንዲከበር የወትሮው ትብብራቸውን እንዲቀጥሉም ነው  የጠየቁት፡፡

በዓሉ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ዲፕሎማቶች፣ ቱሪስቶችና ሌሎቾ እንግዶች  የሚታደሙበት በመሆኑ በጨዋነትና በእንግዳ ተቀባይነት ኢትዮጵያ በዓለም ደምቃና ጎልታ እንድታታይ የምናደርግበት ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡

በተለይም የከተማው ወጣቶች እንደወትሮው ሁሉ በዓሉን ለሌላ አጀንዳ ለመጠቀም የሚፈልጉ ኃይሎችን በጋራ መከላከል ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በኩል በዓሉን ሰላማዊ ሆኖ በድምቀት እንዲከበር በሁሉም መስክ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የገለፁት ዋና ስራ አስኪያጁ ፥ ነዋሪዎችም ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.