Fana: At a Speed of Life!

ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ አይነ-ስውራንን ለመደገፍ የሚደረገውን ዘመቻ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ የሚገኙ አይነ-ስውራን ዜጎችን  ለመደገፍ የሚደረገውን ዘመቻ መቀላቀሉን አስታውቋል፡፡

ሜሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት÷ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አይነ ስውራን  ዜጎችን  ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂጋር በትብብር ለመስራት በመስማማቴ ክብር ይሰማኛል ብሏል፡፡

የኦርካም ቴክኖሎጂ በሺህዎች የሚቆጠሩ አይነ ስውራንን ሕይወት እያሻሻለ መሆኑን ያነሳው ሜሲ÷ ቴክኖሎጂው አይነ ስውራን ህልሞቻቸውን እንዲያሳኩ ይረዳቸዋል ብሏል፡፡

የቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት በቅርቡ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ ኦርካም ማይ አይ የተሰኘ አይነ ስውራንን የሚያግዝ መነጽር ለ2 ሺህ አይነ ስውራን ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

ይህ ዘመናዊ መርጃ መሳሪያ አማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ ያነባል፤ የገንዘብ ኖቶችን ይነግራል፤ ቀለም ይለያል ከፊት ለፊት ምን እንዳለ እና ማን እንደመጣ መዝግቦ በመያዝ መረጃ ይሰጣል፡፡

ኦርካም አይነ ስውራን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ታግዘው የተሻለ ህሕወት እንዲመሩ ለማድረግ የራሱን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ተቋም ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.