Fana: At a Speed of Life!

በተሽከርካሪ ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተሽከርካሪ ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷አደጋው ያጋጠመው በትናትናው ዕለት ምሽት 4 ሰዓት ከ 45 ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ወደ አዳማ የሐበሻ አረቄ ጭኖ እየተጓዘ እያለ አዳማ መዉጫ የመጨረሻ ክፍያ ጣቢያ ሲደርስ ነው ፡፡

በዚህም በተሽከርካሪዎች ውስጥ የነበሩ ሶስት ሰዎች እና አንድ የክፍያ ጣቢያ ትኬት ቆራጭ ሰራተኛ ወዲያው በቃጠሎው ህይወታቸው ማለፉም ነው የተሰማው፡፡

አራት ሰዎችም ከባድ የቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸው በአዳማ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አረቄ ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪና ሌሎች ሦስት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.