Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን አጸዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና የተለያዩ እምነት ተከታዮች የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን አጸዱ፡፡

የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ እንደገለፁት፥ የሃይማኖት አባቶች ተሰባስበን የጥምቀት ማክበሪያ ስፍራን በጋራ ማጽዳታችን ያለንን አንድነትና መተባበርን ያሳየ ነው።

የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱሰላም ጂብሪል ሁሉም ሃይማኖቶች የሰላም ባለቤት በመሆናቸው÷ እኛ የእምነት አባቶችም የሰላም አርዓያ በመሆን የተጀመረውን ሀገራዊ ሰላም ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።

የሐረር ወንጌላዊ አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ጌታሁን ሰላም፥ አብሮነትና አንድነት አስፈላጊ በመሆኑ ይህን ታላቅ እሴት በማጠናከር በዓሉን በጋራ ማክበር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ የተከናወነው የጽዳት ዘመቻ ሐረር የምትታወቅበትን የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት በግልፅ ያሳየ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ጥላሁን ዋደራ ተናግረዋል፡፡

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.