Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓል ጃንሜዳን ጨምሮ በ83 ቦታዎች ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ጃንሜዳን ጨምሮ በሰባት ክፍለ ከተሞች በ83 ቦታዎች ላይ እንደሚከበር የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተገለጸ፡፡

የሀገረስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ለእምነቱ ተከታዮች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፥ በዓሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መሠራቱን ነው ያብራሩት፡፡

በበዓሉ ላይ በርካታ እንግዶች  እንደሚሳተፉ ጠቁመው÷ ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ህብረተሰቡ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤት እና ሌሎች ወጣቶች እንዲሁም መንፈሳዊ ማኅበራት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከጸጥታ ኃይሎች ጎን በመቆም እንዲሠሩም መልዕክት ተላልፏል፡፡

በበዓሉ ቀን ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ   ገልጸዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ እና ቅድስት አባተ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.